በቱሪዝም ሚንስትር ሰላማዊት ካሳ እና በፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ የተመራው የላሊበላ መካነ ቅርስ ጥገና ክትትል ኮሚቴ ዛሬ ምክክር አድርጓል።
ውይይቱ በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ በሚከናወነው የላሊበላ መካነ-ቅርስ የእድሳት ፕሮጀክት ሂደት ላይ ያተኮረ ሲሆን የጥገና ሥራ ጥናትን በተመለከተ የወጣው ዓለም አቀፍ የጨረታ ሂደትና አጠቃላይ የጥገና ሥራውን በተመለከተ በሚደረገው ሳይንሳዊ ጥናት ዙሪያ ዝርዝር ምክክር ተደርጓል:: ሚንስትሯ ሰላማዊት ካሳ የፈረንሳይ መንግስት በቱሪዝም ዘርፍ እያደረገው ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::የላሊበላ መካነ-ቅርስ እንክብካቤ፣ የታላቁ ቤተመንግስት እድሳት እንዲሁም ብሄራዊ ሙዚየምን ለማዘመን የተጀመረውን ስራ … Read more