የቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት መስኮች
01
የቱሪስት መዳረሻ እና መሠረተ ልማት
አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ያለማል፣ ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎለብቱ እና የቱሪዝም ምርት እና አገልግሎት በዓይነትና በመጠን እንዲያድጉ በማድረግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የግል ባለሃብቶችም በልማቱ እንዲሳተፉ ያበረታታል፤
02
የቱሪዘም ገበያ ልማት
የተለያዩ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት የሚያከናውኗቸውን የቱሪዝም ገበያ ፍለጋና ማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስር እና ብራንዲንግ ሥራዎችን በማቀናጀትና በመምራት የአገሪቱን የቱሪዝም ሃብቶች፣ መስህቦችና መልካም ገፅታ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በስፋት ያስተዋውቃል፤ አዳዲስ የቱሪዝም ገበያዎችን ይፈጥራል፣ የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲያድግ ያደርጋል፤
03
የቱሪስት አገልግሎቶች ልህቀት
የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን ይቆጣጠራል፤
ሥልጣኑ በግልጽ በሌላ አካል ካልተሰጠ በስተቀር ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ወይም ህግ በሚፈቅደው አግባብ በውጭ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
04
የተፈጥሮና ባህላዊ ሃብቶች ጥበቃና አጠቃቀም
የሀገሪቱ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
05
ተቋማዊ አቅም ግንባታ
አመራርና ሰራተኞች የእውቀት ክህሎትና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፤ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጣለበትን ተቋማዊ ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ሙያዊ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፡፡
ወቅታዊ ዜና

የዓለም የቱሪዝም ቀን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ መሪ ቃል ይከበራል::
የዓለም የቱሪዝም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ እና በኢትዮጵያ ለ39ኛ ጊዜ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ “የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል

በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ እድገት መመዝገቡና ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።
የቱሪዝም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እያደጉ ካሉ ዘርፎች አንዱ ሲሆን፣ የሀገራትን ኢኮኖሚ በመደገፍ፣ ባህልና ቅርሶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም የሕዝቦች ትስስር እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑ ተገለጻ፡፡ በዓለም

የዓለም ቱሪዝም ቀን 2026
የዓለም ቱሪዝም ቀን 2026 “ዲጂታል አጀንዳ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት – ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” (Digital Agenda and Artificial Intelligence to Redesign Tourism) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ ጊዜ እና በኢትዮጵያ በሀገር
በቱሪዝም ዘርፍ በቅርብ ዓመታት የተሰሩ መዳረሻዎች ለአገር ገጽታ ግንባታ ከመሆንም በላይ አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ መሆን ችለዋል
መንግስት ባለፉት ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት የሀገራችንን ጸጋዎች በመረዳት በማልማት፣ በመጠበቅና በመንከባከብ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሮጅክት ብቻ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ ለምተው በአዲስ መልክ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነዋል