የቱሪዝም ሚኒስቴር ባለፉት ጊዜያት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራቸው ከነበሩ ስትራቴጂክ ስራዎች መካከል 17 አመት የቆየውን የቀድሞ ቱሪዝም ፖሊሲ ማሻል ዋነኛው ነው፡፡
አገራዊና ዓለም አቀፋዊ የቱሪዝም ዘርፍ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በጥልቀት በመተንተን ጊዜውን የሚመጥን የፖሊሲ ሰነድ ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ም/ቤት ፀድቋል፡፡ በፖሊሲው ዝግጅት ወቅት የክልሎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ግብዓት የማይተካ ሚና ነበረው፡፡
ፖሊሲው መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ወሳኝ ትኩረት የሚመጥንና አገራችን ያላትን ፈርጀ-ብዙ የቱሪዝም ፀጋዎች በዘላቂነት በማልማትና በማስተዋወቅ የቱሪዝም እድገትን እውን ለማድረግ የሚያስችለን ወሳኝ ሰነድ፡፡ የቱሪዝምን እድገት የሚፈታተኑ ችግሮችንም ለመፍታት የሚያግዝ የዘርፉ ቁልፍ ሰነድ ነው፡፡
ለቱሪዝም ቤተሰቦችና ለዘርፋችን ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ጥሩ የፖሊሲ ሰነድ መኖሩ ብቻውን የምንፈልገውን ለውጥ ስለማያመጣልን በፖሊሲው ዝግጅት ወቅት ያሳያችሁትን ትብብርና ቁርጠኝነት ፖሊሲውን ወደ ተግባር በመተርጎም ሂደት አጋርነታችሁን ዳግም እንድታረጋገጡ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡
ምንጊዜም ለዘርፉ ልማት ለምታደርጉት ድጋፍና ትብብር ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ከታሪክ ማህደር እስከ ዲጂታል አድማስ
ኢትዮጵያ ያላትን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ፀጋ ለዓለም በበለጠ ጥራት ለማስተዋወቅ አዲስ ምዕራፍ ከፍታለች።
ላለፉት 17 ዓመታት የቆየው አሰራር ተሻሽሎ፣ በዘመናዊነት የታጀበው አዲሱ ብሔራዊ የቱሪዝም ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፅድቋል።
ይህ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ጎዳና ላይ የሚያቆም ሲሆን፣ አምስት ዋና ዋና የለውጥ በሮችን ይከፍታል፦
👉አዳዲስ አማራጮች፦ ከታሪክ ባሻገር የቡና፣ የምግብ (Gastronomy)፣ የጀብዱ እና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
👉ዲጂታል ቱሪዝም፦ ቱሪስቶች አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የሚያሳልጡበት “Smart Destinations” ይፈጠራሉ።
👉የጥራት ደረጃ፦ ከኤርፖርት እስከ መዳረሻዎች ያለው ሰንሰለት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥብቅ የብቃት ማረጋገጫ ይዘረጋል።
👉የግል ዘርፍ ማበረታቻ፦ ለባለሀብቶች የፋይናንስ ተደራሽነትን ማመቻቸትና የቢሮክራሲ ማነቆዎችን ማስወገድ የፖሊሲው አካል ናቸው።
ዘላቂ ልማት፦ ተፈጥሮን የማይጎዳና የአካባቢውን ማህበረሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ አሰራር ይከተላል።
ለምን አስፈለገ?
የቀድሞው የ2001 ፖሊሲ አሁን ያለውን የቴክኖሎጂ ፍጥነትና የቱሪስቶችን ፍላጎት የማይመጥን በመሆኑ፣ ይህ ለውጥ የግድ ሆኗል።
ፖሊሲው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢን እንደሚያስገኝና ለሺዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የታመነበት ሲሆን፣ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታም በላቀ ሁኔታ ይገነባል።
ዘገባው
የኢቢሲ ነው