ታዋቂው ቤልጀማዊ ፎቶግራፈር የፎቶግራፍ መጽሀፍ /Photography Book/ ለቱሪዝም ሚኒስቴር አበረከተ

ኢትዮጵያን ከ20 አመታት በላይ ፎቶግራፍና ቪዲዮ የቀረጸው ታዋቂው ቤልጀማዊ ፎቶግራፈር Olivier Bourguet ያዘጋጀውን መጽሐፍ (Photography Book) እና ዶክመንታሪ ፊልም ለኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በስጦታ አበርክቷል። መጽሀፉ በፈረንሳይኛ ቋንቋ መግለጫ (Photography caption) የያዘ ነው። በዕለቱም የቤልጀም አምባሳደር H.E. Stefaan Thijs እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በቀጣይ መሰል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ፎቶግራፈሮች … Read more

አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ የተራራ ላይ የብስክሌት ጉዞ ፕሮግራም ተካሄደ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከአንኮበር ወረዳ ጀምሮ አስከ አፋር ድረስ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ አላማው ያደረገ የእግር ጉዞ፣ፓራግላዲንግ እና የ16 ኪሎ ሜትር የተራራ ላይ የብስክሌት ጉዞ ተካሄደ።
ፕሮግራሙን ያዘጋጁት በኢትዮጵያ “Ride the rift”በሚል ፕሮግራም ቱሪዝም ሚኒስቴር ከአራት ታዋቂ አስጎብኚ ድርጅቶች ከተስፋ ቱር፣ ዳይናስቲ ኢትዮጵያ ቱርስ፣ሰሜን ኢኮ ቱርስ እና ኢትዮ ሳይክሊንግ ሆሊደይስ ጋር በመሆን ነዉ፡፡
በዚህ ፕሮግራም የቱሪዝም ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ በሃገር ውስጥ የሚገኙ የዉጭ ሃገራት ቆንስላ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች፣አስጎብኚ ድርጅቶችና የቱሪዝም ቤተሰቦች እንዲሁም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተዉጣጡ ከ20 በላይ የሆኑ የብስክሌት ተጓዦች ተሳትፈዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት ለተቸገሩ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸዉ ገቢ የማሰባሰብ በጎ ተግባርም ተከናዉኗል፡፡
ፕሮግራሙ የሀገራችንን በጎ ገጽታ ለመገንባት፣ የቱሪዝም ዘርፍን ለማነቃቃት፣በዘርፉ የተሠማሩ አካላትን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ መስህቦችን ለማስተዋወቅ እና የስፖርት ቱሪዝምን ለማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ተገልጿል፡

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጃው ጂይዋን ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጃው ጂይዋን ጋር በኢትዮጵያ ቱሪዝምን ለማጠናከር እና ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እንደገለጹት ጎብኚዎችን ከአለም አቀፍ ገበያ ለመሳብ ያለውን ጥረት እና የቻይና ቱሪስቶችን ለመቀበል ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል። የውይይቱ ዋና ዓላማ ሁለቱ ሀገራት በቱሪዝም ዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።

የ22ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ተካሄደ

40 ሺህ ተሳታፊዎችን ያስተናገደው ይህ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ ታዋቂ የውጭና የሀገር ውስጥ አትሌቶች ተገኝተዋል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓለም ከሚከናወኑ የጎዳና ላይ ታላላቅ ውድድሮች መካከል ከአፍሪካ በአንደኝነት በዓለም አቀፍ ደግሞ በስድስተኝነት የሚጠቅስ ሲሆን ከኢትዮጵያውያን ባሻገር የተለያዩ የውጭ ቱሪስቶች እና አትሌቶች በተወዳዳሪነት እየተሳተፉበትም ይገኛሉ። … Read more

‘ICCA Skills’ በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ሲሰጥ የቆየው የአምስት ቀናት ስልጠና ተጠናቀቀ።

‘ICCA Skills’ በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ሲሰጥ የቆየው የአምስት ቀናት ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ። የስልጠናው ዓላማ በዓለም አቀፍ የኹነት ዝግጅት ሙያ የዘርፉ ባለሙያዎችን ብቁ የማድረግ እና አለም አቀፍ እውቅና እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ ነው። ሰልጣኞቹ በተሰጠው ስልጠና ጥሩ የሆነ የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ልምድ የቀሰሙ ሲሆን በምላሹም የቢዝነስ ኩነት ዘርፉን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በስልጠናው ላይ … Read more

ቱሪዝም ሚኒስቴር ዘንድሮ የሚካሄደውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለዓለም ማስተዋወቂያ መድረክ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ የቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል። እሁድ የሚካሄደው የ2015 ዓ.ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ተሰጥቷል። የቱሪዝም ሚኒስቴር የገበያ ልማትና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፦ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው አትሌቶች መፍለቂያ ናት ብለዋል። … Read more