ወቅታዊ ዜና

በቱሪዝም ሚንስትር ሰላማዊት ካሳ እና በፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ የተመራው የላሊበላ መካነ ቅርስ ጥገና ክትትል ኮሚቴ ዛሬ ምክክር አድርጓል።
ውይይቱ በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ በሚከናወነው የላሊበላ መካነ-ቅርስ የእድሳት ፕሮጀክት ሂደት ላይ ያተኮረ ሲሆን የጥገና ሥራ ጥናትን በተመለከተ የወጣው ዓለም አቀፍ የጨረታ ሂደትና አጠቃላይ የጥገና ሥራውን በተመለከተ በሚደረገው ሳይንሳዊ ጥናት ዙሪያ

ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም አቅም አደነቁ
ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከአለም አቀፍ ድርጅቶች የተወከሉ ልኡካን የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም አቅም አደነቁ። ኢትዮጵያ የተለያየ ባህል፣ አመጋገብ፣ አልባሳት፣ የተፈጥሮ ጸጋዎችና ታይተው የማይጠገቡ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶችን በስፋት

የጅኦ ቱሪዝም እና ጂኦፓርክ ጽንሰ ሀሳብ በኢትዮጵያና በቀጠናው ለማስተዋወቅ ያለመ ወርክሾፕ እየተካሄደ ነው።
ጂኦፓርክ እና ጂኦ ቱሪዝምን በኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያለውን ግንዛቤ እና ትግበራ ለማጠናከር ያለመ ጉልህ አህጉራዊ ወርክሾፕ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። በወርክሾፕ የመክፈቻ ንግግር ያቀረቡት የቱሪዝም ሚኒሰትር ሰላማዊት ካሳ እንደገለጹት

ኢትዮጵያ የባህሎችና የመልክዓ ምድሮች ባለሕብረቀለም ውህድ ነች። ሰላማዊት ካሳ፦ የቱሪዝም ሚንስትር
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን 2ኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የቅርስ ምርምር ጉባኤ ”ምርምር ለቅርስ ጥበቃና ልማት” በሚል ከድንቅነሽ ግኝት 50ኛ ዓመት መታሰቢያ ጋር በድምቀት ማካሄድ ጀምሯል። የመርሃ ግብሩን ማስጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉት የቱሪዝም ሚኒስቴር

ለጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆኑ ብርቅዬ አትሌቶች ያፈራችው ቦቆጂ ከስፖርት ቱሪዝም ተጠቃሚ እንድትሆን ይሰራል። የቱሪዝም ሚንስቴር
አራተኛ አመቱን ያስቆጠረውና በዘንድሮው የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ’ ተከታታይ ውድድር ሶስተኛ መዳረሻ የሆነችው ቦቆጂ ከተማ ውድድሩን በድምቀት አጠናቀቀች። በአርሲ አባቶች ባህላዊ ምርቃት የተጀመረው የዛሬው ውድድር ከአትሌቶች ጠንካራ ፉክክር ባሻገር የጤና ሯጮች የ12

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የቱሪዝም ዘርፉን እና የሃገር ገፅታን ለመገንባት ያስቻሉ ተግባራት ተፈጽመዋል
በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አሻ ያህያ በቀጣይ በዘርፉ ለዓመቱ ታቅደው ያልተከናወኑ እና አፈጻጸማቸው ዝቅ ያሉ ተግባራትን አማራጭ አፈጻጸም ስልቶችን በመፈለግ እንዲሁም አዳዲስ የመዳረሻ ሥራዎችን
በቱሪዝም ዘርፍ በቅርብ ዓመታት የተሰሩ መዳረሻዎች ለአገር ገጽታ ግንባታ ከመሆንም በላይ አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ መሆን ችለዋል
መንግስት ባለፉት ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት የሀገራችንን ጸጋዎች በመረዳት በማልማት፣ በመጠበቅና በመንከባከብ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሮጅክት ብቻ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ ለምተው በአዲስ መልክ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነዋል
የቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት መስኮች
01
የቱሪስት መዳረሻ እና መሠረተ ልማት
አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ያለማል፣ ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎለብቱ እና የቱሪዝም ምርት እና አገልግሎት በዓይነትና በመጠን እንዲያድጉ በማድረግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የግል ባለሃብቶችም በልማቱ እንዲሳተፉ ያበረታታል፤
02
የቱሪዘም ገበያ ልማት
የተለያዩ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት የሚያከናውኗቸውን የቱሪዝም ገበያ ፍለጋና ማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስር እና ብራንዲንግ ሥራዎችን በማቀናጀትና በመምራት የአገሪቱን የቱሪዝም ሃብቶች፣ መስህቦችና መልካም ገፅታ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በስፋት ያስተዋውቃል፤ አዳዲስ የቱሪዝም ገበያዎችን ይፈጥራል፣ የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲያድግ ያደርጋል፤
03
የቱሪስት አገልግሎቶች ልህቀት
የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን ይቆጣጠራል፤
ሥልጣኑ በግልጽ በሌላ አካል ካልተሰጠ በስተቀር ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ወይም ህግ በሚፈቅደው አግባብ በውጭ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
04
የተፈጥሮና ባህላዊ ሃብቶች ጥበቃና አጠቃቀም
የሀገሪቱ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
05
ተቋማዊ አቅም ግንባታ
አመራርና ሰራተኞች የእውቀት ክህሎትና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፤ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጣለበትን ተቋማዊ ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ሙያዊ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፡፡