Home

አዲስ አባባ
.አፍሪካን ዲፕሎማሲ + ኮንፈረንስ + ንግደና ኤግዚቢሽን ማአከል
የቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት መስኮች

01

የቱሪስት መዳረሻ እና መሠረተ ልማት

አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ያለማል፣ ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎለብቱ እና የቱሪዝም ምርት እና አገልግሎት በዓይነትና በመጠን እንዲያድጉ በማድረግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የግል ባለሃብቶችም በልማቱ እንዲሳተፉ ያበረታታል፤

02

የቱሪዘም ገበያ ልማት

የተለያዩ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት የሚያከናውኗቸውን የቱሪዝም ገበያ ፍለጋና ማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስር እና ብራንዲንግ ሥራዎችን በማቀናጀትና በመምራት የአገሪቱን የቱሪዝም ሃብቶች፣ መስህቦችና መልካም ገፅታ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በስፋት ያስተዋውቃል፤ አዳዲስ የቱሪዝም ገበያዎችን ይፈጥራል፣ የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲያድግ ያደርጋል፤

03

የቱሪስት አገልግሎቶች ልህቀት

የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን ይቆጣጠራል፤

ሥልጣኑ በግልጽ በሌላ አካል ካልተሰጠ በስተቀር ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ወይም ህግ በሚፈቅደው አግባብ በውጭ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤

04

የተፈጥሮና ባህላዊ ሃብቶች ጥበቃና አጠቃቀም

የሀገሪቱ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

05

ተቋማዊ አቅም ግንባታ

አመራርና ሰራተኞች የእውቀት ክህሎትና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፤ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጣለበትን ተቋማዊ ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ሙያዊ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፡፡

ወቅታዊ ዜና

“ከአንኮበር እስከ ሐረር በር”፦ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ6 ከተሞች ውድድር በደብረ ብርሃን በድምቀት ተጀመረ::

የቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና “ከአንኮበር እስከ ሐረር በር” በሚል መሪ ቃል ሀገርን በሩጫ ለማስተዋወቅ የታቀደው የ6 ከተሞች የሩጫ ውድድር ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። በከተማዋ

ለበለጠ መረጃ »

ኢትዮጵያ  የቡና መገኛና የቡና አፈላል ስርዐት በባህላዊ መንገድ ለአለም ያስተዋወቀች ሀገር ናት፡፡

የቡና ስነስርዓት፡ ቡና ኢትዮጵያን አንድ የሚያደረግ የባህላዊ ዕሴት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቡና አፈላል ስነስርዓት፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ማህበረሰባዊ እሴትን እና ትውፊትን የሚያንፀባርቅ የዘመናት ባህል ነው።

ለበለጠ መረጃ »

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትዉልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአስራር” በሚል መሪ ቃል ተከበረ::

የቱሪዝም ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት አመራርና ስራተኞች ጋር በመሆን “ትዉልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአስራር” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ያለውን 22ኛው የጸረ-ሙስና ቀን በዘርፍ ደረጃ አከበረ::

ለበለጠ መረጃ »

በቱሪዝም ዘርፍ በቅርብ ዓመታት የተሰሩ መዳረሻዎች ለአገር ገጽታ ግንባታ ከመሆንም በላይ አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ መሆን ችለዋል

መንግስት ባለፉት ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት የሀገራችንን ጸጋዎች በመረዳት በማልማት፣ በመጠበቅና በመንከባከብ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሮጅክት  ብቻ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ  ለምተው በአዲስ መልክ  ለጎብኚዎች  ክፍት ሆነዋል

ለተፈጥሮ ወዳድ ጎብኚዎች ይምጡ ኢትዮጵያን ይጎብኙ!