ወቅታዊ ዜና

በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባለሙያዎች እና የክልል የባህል እና ቱሪዝም መዋቅር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የቱሪስት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታሪኩ ደምሴ  የቱሪዝም ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማ ጋር በመተባበር በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ

ለበለጠ መረጃ »

ተፈጥሮ ተኮር የቱሪዝም ልማት ሥራዎችን ማስፋት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ ነው

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ተፈጥሮ ተኮር የቱሪዝም ልማት ሥራዎችን ማስፋት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ከአስር ዓመታት በፊት የተቋቋመው የዓለም የዱር እንሰሳት ፕሮግራም ዓመታዊ ጉባኤ

ለበለጠ መረጃ »

ተማሪዎች የሀገራቸውን ቅርስ፣ ታሪክና ባህል የሳይንስ እውቀቶችን በተግባር እንዲያዩ ለማድረግ ያለመ የጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሄደ።

 የቱሪዝም ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 46ተኛ ጊዜ በአገራችን ለ 38ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም ቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በትምህርት ቤቶች ባካሄደው ተንቀሳቃሽ የቱሪዝም ዓውደ-ርዕይ ላይ ተሳትፎ በማድረግ አስተዋፆ ላበረከቱ ተማሪዎች

ለበለጠ መረጃ »

ኢትዮጵያ የዓለም ህዝብ በስስት የሚጎበኛቸዉ፤ ዩኔስኮ ድንቅነታቸዉን የመሰከረላቸዉ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ናት።

የቱሪዝም ሚኒሰትር ክብርት ሰላማዊት የ 38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ በዓይነቱ ለየት ያለ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን በደማቅ ስነ-ስርዓት በዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ተክፈተ።     በመክፈቻ ስነ-ስርዓት

ለበለጠ መረጃ »

ተማሪዎች የሀገራቸውን እምቅ የቱሪዝም ሀብቶች እንዲያውቁ፣ እንዲያደንቁ፣ እንዲመራመሩ እና የጉብኝት ባህላቸውን እንዲያዳብሩ ግንዛቤ ይፈጥራል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ፤ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በሀገራችን ለ38ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም የቱሪዝም ቀንን በማስመልከት “ቱሪዝም ለዘላቂ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በሚገኙ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ሲካሄድ የቆየው ተንቀሳቃሽ የቱሪዝም

ለበለጠ መረጃ »

በቱሪዝም ዘርፍ በቅርብ ዓመታት የተሰሩ መዳረሻዎች ለአገር ገጽታ ግንባታ ከመሆንም በላይ አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ መሆን ችለዋል

መንግስት ባለፉት ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት የሀገራችንን ጸጋዎች በመረዳት በማልማት፣ በመጠበቅና በመንከባከብ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሮጅክት  ብቻ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ  ለምተው በአዲስ መልክ  ለጎብኚዎች  ክፍት ሆነዋል

የቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት መስኮች

01

የቱሪስት መዳረሻ እና መሠረተ ልማት

አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ያለማል፣ ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎለብቱ እና የቱሪዝም ምርት እና አገልግሎት በዓይነትና በመጠን እንዲያድጉ በማድረግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የግል ባለሃብቶችም በልማቱ እንዲሳተፉ ያበረታታል፤

02

የቱሪዘም ገበያ ልማት

የተለያዩ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት የሚያከናውኗቸውን የቱሪዝም ገበያ ፍለጋና ማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስር እና ብራንዲንግ ሥራዎችን በማቀናጀትና በመምራት የአገሪቱን የቱሪዝም ሃብቶች፣ መስህቦችና መልካም ገፅታ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በስፋት ያስተዋውቃል፤ አዳዲስ የቱሪዝም ገበያዎችን ይፈጥራል፣ የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲያድግ ያደርጋል፤

03

የቱሪስት አገልግሎቶች ልህቀት

የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን ይቆጣጠራል፤

ሥልጣኑ በግልጽ በሌላ አካል ካልተሰጠ በስተቀር ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ወይም ህግ በሚፈቅደው አግባብ በውጭ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤

04

የተፈጥሮና ባህላዊ ሃብቶች ጥበቃና አጠቃቀም

የሀገሪቱ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

05

ተቋማዊ አቅም ግንባታ

አመራርና ሰራተኞች የእውቀት ክህሎትና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፤ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጣለበትን ተቋማዊ ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ሙያዊ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፡፡

ለተፈጥሮ ወዳድ ጎብኚዎች ይምጡ ኢትዮጵያን ይጎብኙ!