ወቅታዊ ዜና

ኢትዮጵያ  የቡና መገኛና የቡና አፈላል ስርዐት በባህላዊ መንገድ ለአለም ያስተዋወቀች ሀገር ናት፡፡

የቡና ስነስርዓት፡ ቡና ኢትዮጵያን አንድ የሚያደረግ የባህላዊ ዕሴት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቡና አፈላል ስነስርዓት፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ማህበረሰባዊ እሴትን እና ትውፊትን የሚያንፀባርቅ የዘመናት ባህል ነው።

ለበለጠ መረጃ »

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትዉልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአስራር” በሚል መሪ ቃል ተከበረ::

የቱሪዝም ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት አመራርና ስራተኞች ጋር በመሆን “ትዉልድን በስነ-ምግባር ፤ ተቋምን በአስራር” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ያለውን 22ኛው የጸረ-ሙስና ቀን በዘርፍ ደረጃ አከበረ::

ለበለጠ መረጃ »

ከ40 በላይ አምባሳደሮች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በሀረር ጉብኝት እያደረጉ ነው።

  የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) ላይዘን ቢሮ በመተባበር ያዘጋጁት ከፍተኛ የዲፕሎማቶች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በምስራቅ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ፈርጥ በሆነችው

ለበለጠ መረጃ »

የኢትዮ-ሳውዲ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ተሳታፊ ልዑካን ቤይኑና ኢኮ ሎጅን ጎበኙ!

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ሳውዲ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ተሳታፊዎች፣ በኢትዮጵያ ያለውን የቱሪዝም ዘርፍ ዕድሎችን በቅርበት ለመመልከት እንዲችሉ የቤይኑና ኢኮ ሎጅን ጎበኙ።   በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)

ለበለጠ መረጃ »

ኢትዮጵያ የተወሰዱባትን 12 ውድ ቅርሶች ተረከበች

 ከኢትዮጵያ የተወሰዱ 12 ውድ ቅርሶችን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም ተረክቧል፡፡ ታዋቂው የኒውክሌር ሳይንስ ፕሮፌሰር ራሞን ቫይስ አያታቸው ከ100 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ የጀርመን ልዑክ በነበሩበት ጊዜ በስጦታና

ለበለጠ መረጃ »

የቱሪዝም ፍሰት አፈጻጸም ከእቅድ በላይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላከተ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቱሪዝም ሚኒስቴርን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እየገመገመ ነው።‎‎የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች ጋር

ለበለጠ መረጃ »

በቱሪዝም ዘርፍ በቅርብ ዓመታት የተሰሩ መዳረሻዎች ለአገር ገጽታ ግንባታ ከመሆንም በላይ አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ መሆን ችለዋል

መንግስት ባለፉት ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት የሀገራችንን ጸጋዎች በመረዳት በማልማት፣ በመጠበቅና በመንከባከብ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሮጅክት  ብቻ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ  ለምተው በአዲስ መልክ  ለጎብኚዎች  ክፍት ሆነዋል

የቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት መስኮች

01

የቱሪስት መዳረሻ እና መሠረተ ልማት

አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ያለማል፣ ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎለብቱ እና የቱሪዝም ምርት እና አገልግሎት በዓይነትና በመጠን እንዲያድጉ በማድረግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የግል ባለሃብቶችም በልማቱ እንዲሳተፉ ያበረታታል፤

02

የቱሪዘም ገበያ ልማት

የተለያዩ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት የሚያከናውኗቸውን የቱሪዝም ገበያ ፍለጋና ማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስር እና ብራንዲንግ ሥራዎችን በማቀናጀትና በመምራት የአገሪቱን የቱሪዝም ሃብቶች፣ መስህቦችና መልካም ገፅታ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በስፋት ያስተዋውቃል፤ አዳዲስ የቱሪዝም ገበያዎችን ይፈጥራል፣ የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲያድግ ያደርጋል፤

03

የቱሪስት አገልግሎቶች ልህቀት

የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን ይቆጣጠራል፤

ሥልጣኑ በግልጽ በሌላ አካል ካልተሰጠ በስተቀር ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ወይም ህግ በሚፈቅደው አግባብ በውጭ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤

04

የተፈጥሮና ባህላዊ ሃብቶች ጥበቃና አጠቃቀም

የሀገሪቱ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

05

ተቋማዊ አቅም ግንባታ

አመራርና ሰራተኞች የእውቀት ክህሎትና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፤ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጣለበትን ተቋማዊ ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ሙያዊ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፡፡

ለተፈጥሮ ወዳድ ጎብኚዎች ይምጡ ኢትዮጵያን ይጎብኙ!