‘ICCA Skills’ በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ሲሰጥ የቆየው የአምስት ቀናት ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።
የስልጠናው ዓላማ በዓለም አቀፍ የኹነት ዝግጅት ሙያ የዘርፉ ባለሙያዎችን ብቁ የማድረግ እና አለም አቀፍ እውቅና እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ ነው። ሰልጣኞቹ በተሰጠው ስልጠና ጥሩ የሆነ የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ልምድ የቀሰሙ ሲሆን በምላሹም የቢዝነስ ኩነት ዘርፉን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በስልጠናው ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር የገበያ ልማት ባለሙያዎችና የኢትዮጵያ ኮንቬሽን ቢሮ ባለሙያዎች፣የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ሰራተኞች፣ የኢትዮጵያ ማይስ(MICE)ማህበራት ተሳትፈዋል። አሰልጣኞቹ ከ ICCAWorld (ዓለም አቀፍ ኮንግረስ እና ኮንቬንሽን ማህበር) ናቸው።
መረጃዎቻችንን በትዊተር፡ https://twitter.com/motethiopia
በቴሌግራም፡ https://t.me/tourismethiopia
አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።