አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ የተራራ ላይ የብስክሌት ጉዞ ፕሮግራም ተካሄደ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከአንኮበር ወረዳ ጀምሮ አስከ አፋር ድረስ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ አላማው ያደረገ የእግር ጉዞ፣ፓራግላዲንግ እና የ16 ኪሎ ሜትር የተራራ ላይ የብስክሌት ጉዞ ተካሄደ።
ፕሮግራሙን ያዘጋጁት በኢትዮጵያ “Ride the rift”በሚል ፕሮግራም ቱሪዝም ሚኒስቴር ከአራት ታዋቂ አስጎብኚ ድርጅቶች ከተስፋ ቱር፣ ዳይናስቲ ኢትዮጵያ ቱርስ፣ሰሜን ኢኮ ቱርስ እና ኢትዮ ሳይክሊንግ ሆሊደይስ ጋር በመሆን ነዉ፡፡
በዚህ ፕሮግራም የቱሪዝም ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ በሃገር ውስጥ የሚገኙ የዉጭ ሃገራት ቆንስላ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች፣አስጎብኚ ድርጅቶችና የቱሪዝም ቤተሰቦች እንዲሁም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተዉጣጡ ከ20 በላይ የሆኑ የብስክሌት ተጓዦች ተሳትፈዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት ለተቸገሩ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸዉ ገቢ የማሰባሰብ በጎ ተግባርም ተከናዉኗል፡፡
ፕሮግራሙ የሀገራችንን በጎ ገጽታ ለመገንባት፣ የቱሪዝም ዘርፍን ለማነቃቃት፣በዘርፉ የተሠማሩ አካላትን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ መስህቦችን ለማስተዋወቅ እና የስፖርት ቱሪዝምን ለማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ተገልጿል፡