ታዋቂው ቤልጀማዊ ፎቶግራፈር የፎቶግራፍ መጽሀፍ /Photography Book/ ለቱሪዝም ሚኒስቴር አበረከተ

ኢትዮጵያን ከ20 አመታት በላይ ፎቶግራፍና ቪዲዮ የቀረጸው ታዋቂው ቤልጀማዊ ፎቶግራፈር Olivier Bourguet ያዘጋጀውን መጽሐፍ (Photography Book) እና ዶክመንታሪ ፊልም ለኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በስጦታ አበርክቷል። መጽሀፉ በፈረንሳይኛ ቋንቋ መግለጫ (Photography caption) የያዘ ነው።
በዕለቱም የቤልጀም አምባሳደር H.E. Stefaan Thijs እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በቀጣይ መሰል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ፎቶግራፈሮች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተጠቁሟል።