የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊ ካሳ
“ህይወት በአብያተ መንግስት” በሚል የቀደምት አባቶች፣ ንጉሳዉያን የነበራቸው አኗኗር፣ አለባበስና ይከተሏቸው የነበረ ትውፊቶቸን፣ አስተዳደር ሁኔታ ለሀገር ወስጥና ለውጭ ሀገር ቱሪስትቶች ለማስቃኝት ያለመ ዝግጅት በጎንደር አብያተ-መንግስታት ትዕይንይ ቀረበ።

ዝግጅቱ ብዙ ጥናትቶችን መሰረት አድረጎ ለማሳያነት የቀረበ መሆኑ ተገልጿል ።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊ ካሳ በበኩላቸው የጎንደር አብያተ-መንግስታት በጊዜ ሂደት በእድሜ ብዛትና በተለያዩ ምክንያቶች አደጋ ተጋርጦበት የነበር፣ ነገር ግን በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት ይህ ደንቅ የአለም ቅርሰ የሆነ ሰፍራ ታድሶ በሚያምር ሁኔታ ለትውልድ ማስተላለፍ መቻሉን ገልፀው፤ አሁን ላይ ይህ ደንቅ የሆነ የኪነ ህንጻ ውበት አንዳለ ሁኖ ነብስ አንዝራበት በሚል ሃሰብ “ህይወት በአብያተ መንግስት” ልዪ ዝግጅት መቅረቡ አብራርተዋል።
እንደነዚህ ያሉ ስራዎች በአማረ መልኩ አቅርበን ጎብኚዎች የታሪክ አካል ሆነው ለልጅ ለጆቻቸው የሚናገሩት አድርገን ማስተላለፍ ይገባናል ብለዋል።
በመላው ሀገሪቱ ብዙ ልንናገራቸው ፣ አለም ሊሰማን የሚገባ ሀገሪቱ ብዙ አስደናቂ የሆኑ ታሪኮች አሉን ሲሉ ተናገረዋል።
በዝግጅት የቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታዎች፣ የፌድራል እና የክልል አመራሮች አንዲሁም ሚዲያዎች ተገኝተዋል።
