ወቅታዊ ዜና

የ2018 በጀት ዓመት በተቋም ደረጃ ተፅዕኗችንን ከፍ የምናደርግበት እንዲሆን አቅደን እየሰራን ነው።

ሰላማዊ ካሳ የቱሪዝም ሚንስትር የቱሪዝም ሚኒስቴር የዘርፉን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ 2018 እቅድ “የተናበበ እቅድ የሰመረ ተግባር ፣ ለቱሪዝም ማንሰራራት ” በሚል መሪ ሀሳብ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ በጀመረው

ለበለጠ መረጃ »

በመላ ሀገሪቱ ብዙ ልንናገራቸው ፣ ዓለም ሊሰማን የሚገባ አስደናቂ የሆኑ ታሪኮች አሉን።

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊ ካሳ “ህይወት በአብያተ መንግስት” በሚል የቀደምት አባቶች፣ ንጉሳዉያን የነበራቸው አኗኗር፣ አለባበስና ይከተሏቸው የነበረ ትውፊቶቸን፣ አስተዳደር ሁኔታ ለሀገር ወስጥና ለውጭ ሀገር ቱሪስትቶች ለማስቃኝት ያለመ ዝግጅት በጎንደር አብያተ-መንግስታት ትዕይንይ

ለበለጠ መረጃ »

የሉሲና ሰላም ቅሪተ አካሎች ለታሪክ አጥኚዎች የሚሰጠው ዕድል ትልቅ ነው

የሉሲና ሰላም ቅሪተ አካሎች ለታሪክ አጥኚዎች የሚሰጠው ዕድል ትልቅ ነው አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፡፡ የሉሲ እና ሰላም ኤግዚቢሽን በዛሬው ዕለት በቼክ ሪፐብሊክ ፕራግ ከተማ ክፍት ሆኗል፡፡ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት

ለበለጠ መረጃ »

ብሔራዊ ፓርኮችና በውስጣቸው የሚገኙ የዱር እንስሳት ጥበቃን ይበልጥ በማጠናከር የቱሪዝም ዘርፉን የማሳደግ ተግባር እየተከናወነ ነው

ብሔራዊ ፓርኮችና በውስጣቸው የሚገኙ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት ጥበቃን ይበልጥ በማጠናከር የቱሪዝም ዘርፉን የማሳደግ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ።   አለም አቀፍ የሬንጀሮች ቀን በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተከብሯል። ለተፈጥሮ ሀብት

ለበለጠ መረጃ »

በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰተዋለውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ቪዚት ኢትዮጵያ የዲጅታል መተግበሪያ ለምቶ ለአገልግሎት ቀረበ።

የኢትዮጵያን ቱሪዝም አገልግሎት ዲጂታል የሚያደርግ ቪዚት ኢትዮጵያ የተሰኘ ሀገር በቀል መተግበሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል። በቱሪዝም ዘርፉ በዓለም አቀፍ ገበያ ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ማዘመን አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።   የ

ለበለጠ መረጃ »

የቱሪዝም ሚኒስቴር የ2017 በጀት አመት የ11 ወራት አፈፃፀም ተገምግሞ ዉጤታማ መሆኑ ተገለፀ::

የቱሪዝም ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 ዕቅድ ከሰኔ 7-8 ቀን 2017 ዓ.ም ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች በተገኙበት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተካሂዶበታል። በመድረኩ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት

ለበለጠ መረጃ »

በቱሪዝም ዘርፍ በቅርብ ዓመታት የተሰሩ መዳረሻዎች ለአገር ገጽታ ግንባታ ከመሆንም በላይ አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ መሆን ችለዋል

መንግስት ባለፉት ዓመታት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ትኩረት የሀገራችንን ጸጋዎች በመረዳት በማልማት፣ በመጠበቅና በመንከባከብ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሮጅክት  ብቻ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ  ለምተው በአዲስ መልክ  ለጎብኚዎች  ክፍት ሆነዋል

የቱሪዝም ዘርፍ የትኩረት መስኮች

01

የቱሪስት መዳረሻ እና መሠረተ ልማት

አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦችን ያለማል፣ ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎለብቱ እና የቱሪዝም ምርት እና አገልግሎት በዓይነትና በመጠን እንዲያድጉ በማድረግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የግል ባለሃብቶችም በልማቱ እንዲሳተፉ ያበረታታል፤

02

የቱሪዘም ገበያ ልማት

የተለያዩ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት የሚያከናውኗቸውን የቱሪዝም ገበያ ፍለጋና ማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስር እና ብራንዲንግ ሥራዎችን በማቀናጀትና በመምራት የአገሪቱን የቱሪዝም ሃብቶች፣ መስህቦችና መልካም ገፅታ በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ በስፋት ያስተዋውቃል፤ አዳዲስ የቱሪዝም ገበያዎችን ይፈጥራል፣ የዘርፉን የገበያ ድርሻ እንዲያድግ ያደርጋል፤

03

የቱሪስት አገልግሎቶች ልህቀት

የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ደረጃዎች ይወስናል፣ ተፈጻሚነቱን ይቆጣጠራል፤

ሥልጣኑ በግልጽ በሌላ አካል ካልተሰጠ በስተቀር ከአንድ በላይ በሆኑ ክልሎች ውስጥ አገልግሎት ለሚሰጡ ወይም ህግ በሚፈቅደው አግባብ በውጭ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤

04

የተፈጥሮና ባህላዊ ሃብቶች ጥበቃና አጠቃቀም

የሀገሪቱ የተፈጥሮ ቅርሶች እንዲጠኑ፣ እንዲጠበቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

05

ተቋማዊ አቅም ግንባታ

አመራርና ሰራተኞች የእውቀት ክህሎትና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት፤ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተጣለበትን ተቋማዊ ሃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ሙያዊ ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፡፡

ለተፈጥሮ ወዳድ ጎብኚዎች ይምጡ ኢትዮጵያን ይጎብኙ!