ሰላማዊ ካሳ የቱሪዝም ሚንስትር
የቱሪዝም ሚኒስቴር የዘርፉን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ 2018 እቅድ “የተናበበ እቅድ የሰመረ ተግባር ፣ ለቱሪዝም ማንሰራራት ” በሚል መሪ ሀሳብ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ በጀመረው መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቱሪዝም ሚንስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ በበጀት ዓመቱ በተቋም ደረጃ ተፅዕኗችንን ከፍ የምናደርግበት እንዲሆን አቅደን እየሰራን ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ትኩረት ተሰጥቶባቸው ከተከናወኑ ስራዎች መካከል ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር ትስስር እንዲኖር ማድረግ፤ የቱሪዝም ፖሊሲ ክለሳን ከዳር ማድረስ እንዲሁም ከቱሪዝም ዲጂታላይዜሽን ጋር በተያያዘ የተከናወነው ተግባራትን ውጤታማ እንደነበሩ አንስተዋል።
በ2018 በጀት ዓመት በተቋም ደረጃ ተፅዕኗችንን ከፍ የምናደርግበት እንዲሆን አቅደን እየተሰራ ነው ያሉት ክብርት ሚንስትሯ ለዚህም ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ትስስራችንን ካጠናከርን፤ ስራዎቻችንን በፖሊሲ ደረጃ ካቀድን እና በስትራቴጂ ካስደገፍናቸው እንደ ዘርፍ ኢኮኖሚው ላይ የምናበረክተውን አስተዋጽዖ ከፍ ማድረግ የሚያስችለን ዓመት እንዲሚሆን በአፅንዖት ገልጸዋል።
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ በበኩላቸው ጉባዔው በጅግጅጋ ከተማ መካሄዱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልፀው ከዚህ ቀደም ከፀጥታ ጋር በተያያዘ የዚህን አይነት መድረኮች ማስተናገድ አዳጋች የነበረ ቢሆንም አሁን በተፈጠረው አንፃራዊ ሰላም ከሀገር ውስጥ እንግዶች በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዲያስፖራዎች፣ የጎሮቤት ሀገራት እንግዶች መዳረሻ እየሆነ መምጣቱ ሌላ የታሪክ እጥፋት ነው ሲሉ ገልጸዋል።በተለይ ከሀገር ውስጥ ጉብኝት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የጉብኝት ባህል እየዳበረ የመጣ መሆኑን የገለፁት አቶ ሙስጠፌ በክልል ደረጃ ቱሪዝምን በፅንሰ ሀሳብ ተገንዝቦ ከመስራት አንፃር ጥሩ የሚባል ለውጥ እንዳለ አንስተዋል።
በመጨረሻም የቱሪዝም ሚኒስቴር ጉባዔው በክልሉ እንዲካሄድ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበው ተሳታፊዎች የጉባኤው መጠናቀቅን ተከትሎ በክልሉ የሚገኙ የመሥህብ ስፍራዎች ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የቱሪዝም ዘርፍ የ2017 እቅድ አፈፃጸም እና የ 2018 በጀት ዓመት እቅድ በቱሪዝም ሚኒስቴር የዴሊቨሪ ዩኒት አስተባባሪ በሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ደርበው ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸው በዘርፍ ሚንስትር ዴኤታዎች ክቡር አቶ ስለሺ ግርማ እና እንደገና አበበ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው በመጨረሻም በክብርት ሚንስተር ሰላማዊት ማጠቃለያ ተደርጎባቸዋል።
