በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰተዋለውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ቪዚት ኢትዮጵያ የዲጅታል መተግበሪያ ለምቶ ለአገልግሎት ቀረበ።
የኢትዮጵያን ቱሪዝም አገልግሎት ዲጂታል የሚያደርግ ቪዚት ኢትዮጵያ የተሰኘ ሀገር በቀል መተግበሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።
 
በቱሪዝም ዘርፉ በዓለም አቀፍ ገበያ ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ማዘመን አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።
 
 
 
የ Visit Ethiopia የዲጅታል ፕላትሮርም የማብሰሪያ መርሀግብር ላይ የቱሪዝም ሚንስትር ሰላማዊ ካሳ እንደገለፁት ከአሁን ቀደም በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ውስጥ ከሚስተዋሉ ክፍተቶች አንዱ ጎብኝዎች ስለኢትዮጵያ ቱሪዝም የተሟሉ መረጃዎች በቀላሉ ተዳራሽ ማድረግ አለመቻሉ የነበረ መሆኑን ገልፀው VisitEthiopia የተሰኝ የዲጅታል መተግበሪያ ለምቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ በዘርፍ የሚሰተዋለውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት እንደሚያስችል ጠቁሙዋል ።
 
የቱሪዝም ሚንስትር ወይዘሮ ሰላማዊ ከሳ እንደተናገሩት፤ ቪዚት ኢትዮጵያ መተግበሪያ የቱሪዝም መስህቦችን ወቅታዊ መረጃ በማቅረብ እንዲሁም የዘርፉን ተዋንያን በአንድ መድረክ በማስተሳሰር የአገልግሎት አሰጣጡን ማቀላጠፍ የሚችል ነው ብለዋል።
 
 
ጎብኝዎች የሰመረ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት፣ የጉብኝት ሥፍራዎችንና አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል።
 
መተግበሪያው ከተለያዩ አካላት በርካታ ግብዓቶችን በመውሰድና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቃ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል።
 
የተበታተነ የቱሪዝም አገልግሎት ወደ አንድ መድረክ በማምጣት ማንኛውም ጎብኚ የሚፈልገውን አገልግሎት ሁሉ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ያግዛል ብለዋል።
 
የኢንፎርሜሽን መረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግሥት ሀሚድ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የቱሪዝም ሴክተሩን የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዋንኛ ምሶሶ አድርጎ በመውሰድ ዘርፉን ለማዘመን በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
 
የቪዚት ኢትዮጵያ መተግበሪያ ለቱሪዝም ሴክተሩ ቴክኖሎጂን ተግበራዊ በማድረግ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም አገልግሎት ለማሰጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
መተግበሪያው ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተጠቃሚን መሰረተ ያደረገ የሀገሪቱን የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ የሚያስተዋውቅ ነው ብለዋል።
 
ቴክኖሎጂው ቱሪዝም ሚንስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በትብብር የለማ መሆኑ ተገልጿል።

 

 

Visit Ethiopia ካሉት ፈርጀ-ብዙ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ጠቀሜታዎችን ዉስጥ

የቱሪዝም ፀጋዎችን፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን፣ የቱሪዝም ምርትና አገልግሎቶችን እንዲሁም የኢትዮጵያን ልዩ የቱሪዝም መገለጫዎችን በአንድ Online ስፍራ ለማስተዋወቅ ያስችላል፤

በቱሪዝም እሴት ሰንሰለት ውስጥ የተሰማሩ ቁልፍ የቱሪዝም ተዋንያን በአንድ ስፍራ የሚገናኙበት፣ አገልግሎቶቻቸውንና ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ የሚሸጡበት ከቱሪስቶች ጋር የሚገናኙበት ነው፡፡

ጎብኝዎች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች፣ አገልግሎቶች፣ ምርቶች እና የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች የተመለከቱ ትክክለኛ እና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ያስችላቸዋል፡፡ የጉዞና ጉብኝት ፕሮግራሞችን መርጠው ለመግዛት ወይም የራሳቸውን የጉዞና ጉብኝት ፕሮግራም ለመቅረፅ ይረዳቸዋል፡፡

ፈጣንና ቀላል የBooking ስርዓት ይፈጥራል፡፡ ሁሉም አገልግሎት አቅራቢዎች በአንድ ስፍራ የማግኘት እድል ስለሚሰጥ የጎብኝዎችን አማራጮች ያሰፋል፡፡

ህጋዊ የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ከህገወጦች ለመለየት እና ግልፅና ፍትሃዊ የቱሪዝም ንግድ ለማስፈን ያስችላል፡፡

ለቱሪዝም ዘርፍ ባለድርሻ አካላት አስተማማኝ የቅድመ መረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ጎብኝዎች ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ ስለነበራቸው ቆይታ እና እርካታ ግብረ መልስ የሚሰጡበት ስርዓት አለው፡፡

በጥቅሉ ይህ ፕላትፎርም የኢትዮጵያ ቱሪዝም የዲጅታል ሱቅ/መገበያያ መስኮት ወይም መደብር ነው፡፡