የማንሰራራት ቀን ላይ በቀረቡ አውደ ርዕይ ለእይታ ከቀረቡት መካካል

የማንሰራራት ቀን አስመልክቶ በቀረበው  አውደ-ርዕዩ ላይ  በተለያዩ ዘርፎች የተጠናቀቁ፣ አገልግሎት ላይ የዋሉ ፣ በሂደት ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችንና የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ  በምስልና በመረጃ ቀርበዋል።

ከነዚህን ውስጥ በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የመዳረሻ ልማትና የቅርስ ጥበቃ ስራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም ገቢ ለማሳደግና የአካባቢ ስራ ዕድል ለመፍጠር ያላቸውን ሚና አሳይተዋል። 

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተጠናቀቁ መንገዶች፣ የትራንስፖርት መስመሮችና የሎጂስቲክስ ማዕከላት የሰዎችና የምርቶች እንቅስቃሴን በማቀላጠፍ የገበያ ትስስርን ለማጠናከር የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ተጠቅሷል።

በግብርና ዘርፍ የቀረቡት ስራዎች ምርታማነትን ማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ማጠናከርና የገበሬዎችን ገቢ ማሻሻል ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ደግሞ የማምረት አቅምን በማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን በማስፋፋትና የወጪ ንግድን በማጠናከር ያላቸውን ሚና አሳይተዋል።

በማዕድን ቁፋሮ ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች የተፈጥሮ ሀብትን በህጋዊና በዘላቂ መንገድ በመጠቀም የመንግስት ገቢን ለማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት እድልን ለማስፋፋትና በአካባቢዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ያላቸውን አቅም አስቀምጠዋል።

በከተማ ልማት ዘርፍ የተጠናቀቁ የመኖሪያ፣ የንግድና የህዝብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች የከተሞችን አቀማመጥ ለማሻሻልና የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ለማሳደግ የሚያበረክቱት ሚና ተገልጿል።

በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ዘርፍ የተከናወኑ የኃይል፣ የውሃ፣ የመንገድና የቴሌኮሙኒኬሽን ፕሮጀክቶች የልማት መሠረትን በማጠናከር ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ለህዝብ አገልግሎት መሻሻል ያላቸውን አስተዋፅኦ አሳይተዋል።

በተለይም ተጠናቀው ወደ አገልግሎት የገቡ ፕሮጀክቶች የልማት ግቦች በተጨባጭ ወደ ህዝብ እንዴት እየደረሱ እንደሆነ እንደ ማሳያ ቀርበዋል።