ኢትዮጵያ የዓለም ህዝብ በስስት የሚጎበኛቸዉ፤ ዩኔስኮ ድንቅነታቸዉን የመሰከረላቸዉ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ናት።

የቱሪዝም ሚኒሰትር ክብርት ሰላማዊት

የ 38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ በዓይነቱ ለየት ያለ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን በደማቅ ስነ-ስርዓት በዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ተክፈተ።
 
 
በመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒሰትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ አንደገለጹት የዛሬ ተማሪዎች የነገ በሁሉም መስክ ሀገራቸውን የሚያገለግሎ ዜጎች በመሆናቸው ስለ ሀገራቸው የባህል፣ የታሪክ፣ ተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶች እንዲያውቁ እና ሀገሩን የሚውድ ትውልድ ለመፍጠር ተንቀሳቀሽ አውደ ርዕይ እንደተዘጋጀ አንስተው ኢትዮጵያ የዓለም ህዝብ በስስት የሚጎበኛቸዉ፤ ዩኔስኮ ድንቅነታቸዉን የመሰከረላቸዉ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል።
 
 
ዛሬ በይፋ በዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ ለጉብኝት ያቀረብናቸው እና በቀጣዩ ሳምንታትም በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በጄ.ታደሰ ብሩ ት/ቤት በመጨረሻም በቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለእይታ እንደሚቀርቡ ጠቁመዋል።
 
ይህ ዝግጅት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና ተባባሪ በሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን አንደተዘጋጀ ተገልጿል ።
 
 

38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀን

ኢትዮጵያ የዓለም ህዝብ በስስት የሚጎበኛቸዉ፤ ዩኔስኮ ድንቅነታቸዉን የመሰከረላቸዉ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ናት።
የ 38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጅ በዓይነቱ ለየት ያለ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን
ለበለጠ