የኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲስ ምዕራፍ፦ ከገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ

የቱሪዝም ሴክተር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ ካሉት ከአምስቱ ቁልፍ ምሠሦዎች አንዱ ሆኖ የተቀመጠ ሲሆን፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዘርፉን ለማሳደግ ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ ለውጦች ተደርገዋል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳቢነት የተጀመሩት “ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻዎች በማስፋት፣ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ፀጋዎችን በማልማት ረገድ አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል። እነዚህ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከማሳደግ ባለፈ፣ ዘርፉ ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ያለውን ፋይዳ ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረውታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ቱሪዝምን ካስቀመጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ በማድረግ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዘርፉን ለማሳደግ ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ ለውጦች ተደርገዋል። በተለይም በሦስቱ የ“ገበታ” መርሃ-ግብሮች አማካኝነት የተገነቡት መዳረሻዎች ለጎብኚዎች ልዩ ተሞክሮን የሚሰጡ ናቸው።

ገበታ ለሸገር የአዲስ አበባን ገጽታ በመቀየር ለቱሪስት ምቹና አረንጓዴ ከተማ እንድትሆን አስችሏል።

ዋና ዋና መዳረሻዎች፦ የአንድነት ፓርክ፣ ወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ፓርክ እና የሳይንስ ሙዚየም ይገኙበታል፡፡

ታሪክና ተፈጥሮ በአንድ ቅጥር ግቢ!

የኢትዮጵያን የዘመናት የቤተ-መንግሥት ታሪክ መቃኘት ይፈልጋሉ? የአንድነት ፓርክ የታሪክ መዘክሮችን፣ የንጉሳውያን መኖሪያዎችን እና አስደናቂውን የእንስሳት ማቆያ በአንድ ላይ የያዘ ድንቅ ስፍራ ነው።

ፓርኩ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት፣ የጥቁር አንበሳ ማቆያ እና የክልሎች ድንቅ የባህል አውደ-ርዕዮች አሉት።

ፓርኩ ለታሪክ ጥናት፣ ለቤተሰብ ሽርሽር እና ለሀገራዊ ኩራት ሊጎበኙት ይችላሉ።

መገኛ፦ ታላቁ ቤተ-መንግሥት (አዲስ አበባ)።

የከተማዋ እምብርት ላይ ያለ ገነት!

በአዲስ አበባ እምብርት ላይ ሆኖ ሰላምንና መረጋጋትን የሚያገኝበት ውብ ስፍራ። ዘመናዊ የውሃ ዳንስ (Water Fountain) ፣ አረንጓዴ ስፍራዎች እና ለዓይን ማራኪ የሆኑ የአበባ ዲዛይኖች መገኛ።

በስፍራው አስደናቂውን የሰው ሰራሽ ሐይቅ፣ የውሃ ላይ ዳንስ እና ሰፊውን የመሰብሰቢያ አደባባይ ይጎበኛሉ ። በተለይ ለሠርግ ፎቶዎች፣ ከጓደኞች ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እና በምሽት የውሃ ዳንስ ለመዝናናት ልዩ ቦታ ነው።

መገኛ፦ አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት  ፊት ለፊት።

ለንጹህ አየር እና ለጀብዱ አፍቃሪዎች!

ከከተማዋ ጫጫታ ርቀው ንጹህ የአየር እስትንፋስ የሚወስዱበት፣ በተፈጥሮ ደን የተከበበ ስፍራ። ከስፖርት እስከ ከፍተኛ ደረጃ መዝናኛዎች ሁሉንም በአንድ ቦታ ያገኛሉ።

ከቤት ዉጭ ለሚደረጉ የቱሪስት እንቅስዋሴዎች ለምሳሌ የብስክሌት ግልቢያ፣ የቀስት ውርወራ፣ የጫካ ውስጥ የእግር ጉዞ (Hiking) እና የፈረስ ግልቢያ እንዲሁም

ለጤናማ እንቅስቃሴ፣ ለተራራ ላይ እይታ (City View) እና ለልዩ ምግቦች ያገኛሉ።

መገኛ፦ እንጦጦ ተራራ።

ወደፊቱ ዓለም የሚወስድ የዕውቀት በር!

የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ጉዞ እና የሰው ልጅ የፈጠራ ውጤቶችን በአንድ ላይ የሚያሳየው፣ በቅርጹም ሆነ በይዘቱ ልዩ የሆነው የሳይንስ ሙዚየም!

በውስጡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ፣ የሮቦቲክስ ትርኢቶች እና ወቅታዊ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ያካተተ፤ ለዕውቀት፣ ለልጆች የፈጠራ ተነሳሽነት እና ለቴክኖሎጂ አድናቂዎች ጎራ በሉ።

መገኛ፦ በአዲስ አበባ እምብርት፣ ወዳጀነት ፓርክ አጠገብ

ይህ መርሃ-ግብር ትኩረቱን ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የተፈጥሮ ፀጋዎች ላይ በማድረግ  ግዙፍ መዳረሻዎችን እያለማ ይገኛል።

ተፈጥሮ በምድራዊ ገነትነት የተገለጠችበት – ወንጪ!

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የወንጪ-ድንዲ ፕሮጀክት፣ የእሳተ-ገሞራ ፍንዳታ ውጤት የሆኑትን ውብ ሐይቆች፣ የተፈጥሮ ደኖችንና ፏፏቴዎችን ለጎብኚዎች በሚመች መልኩ አዘምኖ ይዟል። በሐይቁ ላይ የጀልባ ሽርሽር፣ አረንጓዴ የደን ጉዞ እና የፈረስ ግልቢያ ይመረጣል።

የወንጪ-ድንዲ ለኢኮ-ቱሪዝም አፍቃሪዎች፣ ለጫጉላ ጊዜ እና ለፈታኝ የእግር ጉዞ (Hiking) ወደር የማይገኝለት ስፍራ ነው።

መገኛ፦ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ (ከአዲስ አበባ 155 ኪ.ሜ ርቀት)።

 የታሪክና የውሃ ዳርቻ ውበት ጥምረት – ጎርጎራ!

በታሪካዊቷ ጎንደር አቅራቢያ በጣና ሐይቅ ዳርቻ የተገነባው የጎርጎራ ፕሮጀክት፣ የሰሜኑን ታሪካዊ መስመር ከዘመናዊ የውሃ ዳርቻ መዝናኛ ጋር ያገናኘ ድንቅ ሥራ ነው። የጣና ሐይቅን የውሃ ላይ እይታ፣ ዘመናዊ የሪዞርት አገልግሎት እና ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናትን ለመጎብኘት ብሎም

የመዝናኛ ማዕከላትና የወደብ ልማቱ ለውሃ ላይ ቱሪዝም ምቹ ያደርገዋል። ለውሃ ላይ ስፖርት፣ ለወፍ ዝርያዎች ምልከታ እና በታሪክ ጥላ ስር ሆኖ ለመዝናናት ተመራጭ  ሪዞርት አሉት ይጎብኙ ይዝናኑ ።

መገኛ፦ ደቡብ ጎንደር፣ ጣና ሐይቅ ሰሜናዊ ዳርቻ።

የዱር እንስሳትና የተፈጥሮ ድንቅ ስራ – ኮይሻ!

በኦሞ ወንዝ ተፋሰስና በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ አቅራቢያ የሚገኘው የኮይሻ ፕሮጀክት፣ ኢትዮጵያ ያላትን ያልተነካ የተፈጥሮ ፀጋ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ታላቅ መዳረሻ ነው።

የተፈጥሮ ደንና የዱር እንስሳትን ለማየት የሚመረጥ ልዩ ስፍራ ነው። የዝሆኖችን ጉዞ፣ የኦሞ ወንዝን አስደናቂ እይታ እና በአፍሪካ ግዙፍ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነውን ግድብ ያገኛሉ።

ኮይሻ ለሳፋሪ ጉብኝት፣ ለዱር እንስሳት ፎቶግራፍ እና ጥንታዊ ባህሎችን ለማየት ልዩ ዕድል ይሰጣል።

መገኛ፦ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮይሻ አካባቢ።

ይህ ዙር የቱሪዝም መዳረሻዎችን ይበልጥ በማስፋትና የቆዩ ቅርሶችን በማደስ ላይ ያተኩራል።

ዋና ዋና መዳረሻዎች፦ የዓድዋ ድል መታሰቢያ (አዲስ አበባ)፣ የደንቢ ተፈጥሮ ፓርክ ፣ ቤኑና መንደርሽበሌ ሪዞርትሎጎ ሀይቅፋሲል ግቢ እና ሌሎች በየክልሉ ያሉ ስፍራዎች።

 በመንግሥትና በዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች (በተለይም በፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍ) እየተከናወነ ያለው የእድሳት ሥራ፣ ቅርሱ የነበረውን ጥንታዊ ገጽታ ሳይለቅ በዘመናዊ የጥበቃ ዘዴ እንዲታደስ እያደረገ ነው።

የፋሲል ግቢ (የጎንደር ግንቦች) የኢትዮጵያ የታሪክ፣ የጥበብና የሥልጣኔ መገለጫ ከመሆኑም ባለፈ በዩኔስኮ (UNESCO) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ኩራታችን ነው። ይህንን ታላቅ ቅርስ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተከናወነ ያለው የእድሳት ሥራ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ አዲስ ተስፋን የፈነጠቀ ነው።

ፋሲል ግቢ ጥንታዊነትን መጠበቅ (Conservation) የእድሳት ሥራው ቅርሱ የተገነባበትን ጥንታዊ ድንጋይ፣ ኖራና እንጨት ሳይቀይር፣ በነበረው የጥበብ ዘዴ (Authenticity) ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

ከጎብኚዎች ደህንነትና ምቾት አንጻር  በእርጅና ምክንያት ሊናዱ የሚችሉ ግንቦችን በማጠናከር፣ ጎብኚዎች በሰላም ተዘዋውረው እንዲመለከቱ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

በግቢው ውስጥ ያሉ አረንጓዴ ስፍራዎችና መንገዶች ከታሪካዊ ግንቦቹ ጋር በሚስማማ መልኩ ተዘጋጅተዋል፡፡

ፋሲል ግቢ የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ስነ-ህንፃ፣ ስነ-መንግሥትና ባህል መማሪያ ትልቅ ሙዚየም ነው። እድሳቱ መጠናቀቁ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በቆይታቸው እንዲደሰቱና የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲያድግ ያደርጋል። የጎንደር ከተማ የቱሪስት መዳረሻነቷን ይበልጥ በማጠናከር፣ ለሆቴሎች፣ ለ አስጎብኚዎችና ለባህላዊ እደ-ጥበብ ባለሙያዎች ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

ፋሲል ግቢ “የታሪክ ኩራታችን ነው!

ጎንደርን ሲጎበኙ የታሪክን አሻራ በአዲስ መልክ ለመመልከትና የነገሥታቱን ጥበብ ለመቃኘት አይርሱ! የፋሲል ግንብ፣ የኢያሱ ግንብ፣ የቤተ-መንግሥቱን ቤተ-መጻሕፍትና ድንቅ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ይመለከታሉ።

ኢትዮጵያን ይጎብኙ፤ የታሪክ ባለቤት ይሁኑ!

 በምሥራቅ ሸዋ ዞን በፈንታሌ ወረዳ፣ በታሪካዊውና ውብ በሆነው የበሰቃ ሐይቅ ዳርቻ ላይ የተገነባ ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው። ይህ መንደር የ“ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክት አካል ባይሆንም፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳቢነትና በግል ባለሀብቶች ቅንጅት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ትኩረት በተሰጠበት ወቅት የተገነባና የኢትዮጵያን የመስተንግዶ ጥበብ ከፍ ያደረገ ስፍራ ነው።

ቤኑና መንደር (Benuna Village) ፦ በበሰቃ ሐይቅ ላይ የበቀለች ዕንቁ!

በአዲስ አበባ እና በናዝሬት (አዳማ) አቅራቢያ ለየት ያለ የዕረፍት ጊዜ ማሳለፍ ይፈልጋሉ? ቤኑና መንደር የተፈጥሮን ውበት፣ ዘመናዊ ምቾትን እና የቆየውን የአካባቢውን ባህል አውህዶ የያዘ ድንቅ የቱሪስት መዳረሻ ነው።

 ቤኑና ተፈጥሮአዊ ድባብ በበሰቃ ሐይቅ ሰማያዊ ውሃ እና በፈንታሌ ተራራ ግርማ ሞገስ የታጀበው  መንደር ሲሆን ለዓይን ማራኪ እና ለነፍስ እረፍት የሚሰጥ ነው።

የመንደሩ ቤቶች የተገነቡት ከአካባቢው እሳተ-ገሞራ ድንጋዮችና ከባህላዊ ቁሳቁሶች በመሆኑ፣ ከቦታው ተፈጥሮ ጋር ፍጹም ተስማምተው ይታያሉ።

በሐይቁ ዳርቻ የእግር ጉዞ ማድረግ ለሚፈልጉ ጎብኝዎች፣ በፀጥታ ውስጥ መጽሐፍ ማንበብ፣ እና የምሥራቁን ሐሩር አየር እየተነፈሱ በዘመናዊ መስተንግዶ መደሰት ለሚፈልጉ ልዩ ስፋራ  መዳረሻ ነው፡፡

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት (መተሃራ አካባቢ) የሚገኝ በመሆኑ፣ ለሳምንት መጨረሻ (Weekend) ዕረፍት ተመራጭ ያደርገዋል።

ለቤተሰብ፣ ለጓደኛማቾች እና ለሥራ ስብሰባዎች (Retreat) ፍጹም ተስማሚ ነው። ለፎቶግራፍ ወዳድ  ሰዎች ፀሐይ ስትጠልቅ (Sunset) በሐይቁ ላይ የሚታየው ነጸብራቅ ለማይረሳ ፎቶግራፍ ድንቅ ዕድል ይፈጥራል።

የደቡብ ወሎው ዕንቁ የሆነው ሎጎ ሐይቅ (Logia/Hayq) እና በአካባቢው የሚገኙት እንደ ሎጎ ኃይቅ ሪዞርት እና ሰበሌ ሪዞርት ያሉ የቱሪስት በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶችን ሲያስጀምሩ፣ እንደ ሎጎ ሐይቅ ያሉ ተፈጥሯዊ ፀጋዎች ከዘመናዊ የመሠረተ ልማት ግንባታ ጋር ተዳምረው የሰሜኑን የቱሪስት መስመር (Northern Tourism Circuit) የሚያነቃቁ መዳረሻዎች ናቸው፡፡

ሎጎ ሐይቅ ከደሴ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ፣ በጥንታዊው የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም የሚታወቅና አሁን ላይ ደግሞ በዘመናዊ ሪዞርቶች እየደመቀ ያለ ስፍራ ነው።

በሐይቁ ለሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ምቹና ዘመናዊ መስተንግዶን በማቅረብ ቀዳሚ ነው።

ሪዞርቱ የሐይቁን ሙሉ እይታ (Panoramic View) የሚያሳይ ሰፊ በረንዳ ያለው ሲሆን፣ የውሃ ላይ ጀልባ ሽርሽርና ትኩስ የሐይቅ ዓሳ ምግብ በዋናነት የሚታወቅበት ነው።

የሪዞርቱ መገንባት  ለቤተሰብ ዕረፍትና ለሥራ ስብሰባዎች (Conferences) ምቹ በመሆኑ በደቡብ ወሎ ዞን ያለውን የቱሪዝም ፍሰት በእጅጉ ጨምሮታል።

በሎጎ ኃይቅ ሪዞርት የዓሳ ምግብ እየተመገቡ በጀልባ መዝናናት፣ አሊያም  ሪዞርት ዘመናዊ መስተንግዶ ማግኘት አሁን ቀላል ሆኗል። ተፈጥሮና ዘመናዊነት የተገናኙበትን ይህን ድንቅ ስፍራ ሳይጎበኙ እንዳያልፉ!

በሶማሌ ክልል የሚገኘው ሽበሌ ሪዞርት (Shebelle Resort) በክልሉ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ አዲስ ተስፋ ይዞ የመጣ ግዙፍና ዘመናዊ መዳረሻ ነው። ይህ ሪዞርት በተለይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ ከዘመናዊ መስተንግዶ ጋር በማቀናጀት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ምቹ ሆኖ ተገንብቷል።

በታሪካዊውና ግዙፉ የዋቢ ሽበሌ ወንዝ ተፋሰስ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ ሪዞርት፣ የሶማሌ ክልልን የቱሪዝም ገጽታ በአዲስ መልክ እየቀየረ ይገኛል። ሪዞርቱ ለክልሉ የኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

ሪዞርቱ በዋቢ ሽበሌ ወንዝ ግርማ ሞገስ የታጀበ በመሆኑ፣ ጎብኚዎች የወንዙን ለምለም ዳርቻና የተፈጥሮ አየር እየተነፈሱ እንዲያርፉ ያስችላል። ዘመናዊ ስነ-ህንፃ፦ የሪዞርቱ ግንባታ የሶማሌን ባህላዊ ቤት አሠራር (Somali Traditional Hut) ከዘመናዊ የቅንጦት ሆቴል አሠራር ጋር ያዋሃደ ነው።

ሪዞርቱ ሰፊ የዋና ገንዳ (Swimming Pool) በወንዙ ዳርቻ የሚደረግ የጀልባ ሽርሽር።

የሶማሌን ባህላዊ ምግቦችና ዓለም አቀፍ ምግቦችን የሚያቀርቡ ዘመናዊ ምግብ ቤቶች።

መዳረሻው በክልሉ ያለውን አስተማማኝ ሰላም እና ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑን ለዓለም የሚያሳይ ትልቅ ፕሮጀክት ነው።

በዋቢ ሽበሌ ወንዝ ዳርቻ ላይ የተገነባው ድንቅ መዳረሻ ሽበሌ ሪዞርት አሁን ለጉብኝት ክፍት ነው። የሶማሌን ሞቃታማ አየር በወንዙ ዳርቻ አረንጓዴ ተፈጥሮ እያቀዘቀዙ፣ በዘመናዊ ሪዞርት ውስጥ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፉ። ለቤተሰብ ዕረፍት፤ ለጫጉላ ሽርሽር፤ ለሥራ ስብሰባዎችና ለሪትሪት (Retreat) ክፍት ነው፡፡

የሶማሌ ክልልን እንግዳ ተቀባይነት በሽበሌ ሪዞርት ይለማመዱ!

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካለችበት የፖሊሲ ትኩረት አንጻር፣ እነዚህ መዳረሻዎች በቴክኖሎጂ የተደገፉና ደህንነታቸው የተጠበቀ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። እነዚህ የመሰሉ መዳረሻዎች መበራከታቸው በቱሪዝም ሴክተሩ የተጀመረው የፖሊሲ ለውጥ ውጤት ነው።

መንግሥት የመሠረተ ልማት (መንገድ፣ መብራት) ሲያመቻች፣ የግል ባለሀብቱ እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎችን በመገንባት የሀገርን ገጽታ መቀየር እንደሚችል ትልቅ ማሳያ ነው።

እንዲህ ያሉ ፕሮጀክቶች ለአካባቢው ማህበረሰብ የሥራ ዕድል ከመፍጠራቸውም በላይ፣ ቱሪዝም የኢኮኖሚው ምሶሶ እንዲሆን ያግዛሉ።