የጳጉሜ 2 “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” መሪ ቃልን መነሻ በማድረግ በተካሄደው ሀገራዊ የፓናል ውይይት ላይ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች የምታስመዘግበው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትና የልማት ውጤቶች ተዳሰዋል።
በቱሪዝም፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ ከተማ ልማት እንዲሁም ውሃና ኢነርጂ ዘርፎች ላይ ያተኮረው ይህ ውይይት፣ ሀገሪቱ የያዘችውን አዲስ የዕድገት መንገድ አሳይቷል።
በፓናል ውይይቱ ወቅት እንደተመላከተው፣ የቱሪዝም እና የአየር ትራንስፖርት/ሎጂስቲክስ ዘርፎች እርስ በእርስ ተጋገዘው ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ማሰለጫ ዋና አዕማድ በመሆን እየተሰራባቸው እንደሆነ ተነሰቷል።

በፓናሊስቶቹ ገለጻ መንግሥት የሚገነባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ለግሉ ዘርፍ አርአያ የሚሆኑ በመሆናቸው፣ ሀገራዊ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደጉት እንደሚገባ አንስተዋል።
የዚህ ሀገራዊ ማንሰራራት ሁነኛ ማሳያ ተደርጎ የቀረበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ የአቪዬሽንና የሎጂስቲክስ ዘርፉን ወደ አዲስ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ጠቀሰዋ።
ይህ ግዙፍ የአየር ማረፊያ ግንባታ ሀገሪቱ በቱሪዝም፣ በንግድና በትራንስፖርት ዘርፍ ያላትን ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት የሚያጎለብት በመሆኑ፣ በጳጉሜ 2 የፓናል ውይይት ላይ ለተነሳው “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” ራዕይ በተግባር የተረጋገጠ አምሳያ መሆኑ ተገልጿል።
