የቱሪዝም ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 ዕቅድ ከሰኔ 7-8 ቀን 2017 ዓ.ም ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች በተገኙበት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተካሂዶበታል።
በመድረኩ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በ2017 በጀት አመት የተገኘዉ ዉጤት ጥሩ ጅምር መሆኑን እና የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እና የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞችና አመራር የጋራ የተቀናጀ ጥረት የተገኘ ዉጤት መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በ2017 በጀት አመት የተጀመሩ የአገልግሎት ጥራት፣ የዲጂታል ፕሮሞሽን፣ የኮንፈረንስ ቱሪዝም፣ የመዳረሻ ልማት፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት እና መሰል የለውጥ ስራዎችን በማስቀጠል በቀጣይ አመት ለበለጠ ውጤት መትጋት እንደሚገባ በአፅንኦት አንስተዋል።
በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ በዶ/ር እንደገና አበበ የ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚ/ር ድኤታ በዝርዝር ቀርቦ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁሉም ሰራተኞች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ከመዳረሻ ልማት አንፃር የተከናወኑ ስራዎች እና ቀጣይ ዕቅዶችን በተመለከተም በአቶ ስለሺ ግርማ የመዳረሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ በኩል ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጥቷል::

የተቋሙ የስራ አስፈጻሚዎች በበጀት አመቱ የተከናወኑ ስራዎች በቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች መመዘኛ መስፈርት መሰረት መገምገማቸዉ የዘርፉን ሁለንተናዊ ፋይዳ ለመረዳት፣ ለክትትልና ቁጥጥር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለዉ መሆኑን አብራርተዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው በበጀት አመቱ በሀገር ዉስጥ ቱሪዝም፣ በርካታ አለምዓቀፍ ኹነቶችን በማስተናገድ፣ በፕሮሞሽን፣ የመዳረሻ ልማት፣ የአገልግሎት ጥራት ደረጃ ምደባ እና ዲጂታይዜሽን ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ከነበረዉ ዕቅድ አንጻር ሲታይ አመርቂ መሆኑን እና በቀጣይ ጊዜም ከባለድርሻ አካላትና ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ መስራት መሰል ዉጤት ለማስመዝገብ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም በቀጣይ በጀት አመት ሁሉም የተቋሙ የስራ ክፍሎች በእቅዱ መሰረት ለዘርፉ ስኬት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል::
ከዕቅድ አፈጻጸሙ ግምገማ ጎን ለጎን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሰራተኞች እና አመራሮች በመካከለኛዉ ስምጥ ሸለቆ (Central Rift Valley) የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ማለትም የላንጋኖ ሀይቅ እና ሪዞርት፣ የአቢጃታ ሻላ ፓርክ፣ በዝዋይ/ባቱ የሚገኘዉን የወይን እርሻ እና ቅምሻ ማዕከል/Wine testing center የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ጎብኝተዋል።