ቱሪዝም ሚኒስቴር ለአምስት ቀናት የቆየ “የቡና ቱሪዝም” (Coffee Tourism) የተሰኘ ስትራቴጂካዊ የሚዲያ ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡ ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና (Coffea arabica) መገኛና የቡና አፈላል ስርዐት በባላዊ መንገድ ለአለም ያስተዋወቀች ሀገር ናት፡፡

ኢትዮጵያ የማያጠራጥር የቡና መገኛ ሀገር ናት። ታሪኳም ከዘመናት በፊት ቀይ የቡና ፍሬዎችን ካገኘው ፍየል ጠባቂው ካልዲ አፈ ታሪክ አንስቶ፣ ዛሬም ድረስ በኢትዮጵያውያን ማህበራዊ እና ባህላዊ ህይወት ውስጥ ደማቅ ወበት ያለው የባህላዊ እሴት መገለጫ ነው፡፡
የቡና ቱሪዝም ልምድ
ቡና ለኢትዪጵያን የእንግዳ ተቀባይነት መገለጫ ነው፡፡ አዲስ እንግዳ ወደቤታቸው ሲመጣ በባህላዊ የብና አፍላል ስርዓት አዘጋጅተው ይቀበላሉ፡፡
ቡና ዛሬም ድርሰ በዘመናዊ መንግድ የንግድ ሰዎች የቢዝነስ ሃሳብ ለመለዋወጥ፤ ዘመድ ወዳጅ ጓደኞች ተገናኝተው ለመመካከር ቡና አፍልተው በዙሪያው ይመክራሉ፡፡
ኢትዮጵያን ከብና ጋር ባላቸው ቁርኝት ቤተሰብ ወደ ስራ ከመሄዱ በፊት ጠዋት ቡና አፍልተው በእለት ጉዳያቸው ይወያዩበታል፣ የሀገሬው ሰው የባህላዊ ዕርቅ ሽምግልና ስርዓት ለመከውን ቡና አፍልተው ተጠራርተው ይታደሙታል፡፡
በዛሬው የቡና ቱሪዝም ጉዞ ልምድ ለመካፍል በቡና አምራችነታቸው ወደ ታወቁት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማለትም ጂማ፣ ካፋ፣ ሲዳማ እና ይርጋጨፌ በመውሰድ በቡና እርሻ፣ ምርት መሰብሰብ እና ማዘጋጀት ሂደት ላይ ጥልቅ ልምድ እንዲቀስሙ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ቡናን ልዩ ጥራት እና ለአለም አቀፍ ዝናው ምክንያት የሆነውን የላቀ ጣዕም በቦታው ተገኝተው ልዪ ጥራትና ቃና በላቀ ጣዕም ይጠጣሉ፡፡
የቡና ስነስርዓት፡
ቡና ኢትዮጵያን አንድ የሚያደረግ የባህላዊ ዕሴት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቡና አፈላል ስነስርዓት፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ማህበረሰባዊ እሴትን እና ትውፊትን የሚያንፀባርቅ የዘመናት ባህል ነው።
የቡና ስርዓት ከቦታ ቦታ የራሱ የሆነ ልዩ ውበት ያለው ደማቅ የማህበራዊ ዕሴት ነው፡፡ የቡና አፋላል ስዓርት ሶስት ዙር የባህላዊ ሂደት ተከትሎ ይከውናል፡፡ ባህላዊ ሂደቱ እንግዶች ከቡና ቆሎ ጀምሮ እስከ አቦል፣ ቶና እና በረካ (ሶስት ባህላዊ ዙሮች) ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን ዘላቂ የባህል ቅርስ የሚያሳይ ሙሉ ስነስርዓት አለው።
የቱሪዝም ሚኒስቴር የአለም አቀፍ ሚዲያ አካላት፣ የጉዞ ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የባህል እና የምግብ ቱሪዝም ባለድርሻ አካላት በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ እና የኢትዮጵያን የበለፀገ የቡና ቅርስ ለአለም አቀፍ ታዳሚዎች እንዲያስተዋውቁ ያበረታታል።




