የቱሪዝም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እያደጉ ካሉ ዘርፎች አንዱ ሲሆን፣ የሀገራትን ኢኮኖሚ በመደገፍ፣ ባህልና ቅርሶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም የሕዝቦች ትስስር እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑ ተገለጻ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተፈጠሩት የሥራ ዕድሎች መካከል አንዱ በቱሪዝም ሴክተር ምክንያት የተፈጠረ መሆኑም ተመላክቷል።

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ክብርት ሰላማዊት ካሳ እንደገለጹት፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የውጭ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን፣ ከዘርፉም ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
ይህም ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ300 ሺህ በላይ ጎብኚዎች እና ከ21% በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ጭማሪ ማሳየቱን አብራርተዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመስከረም እና የጥቅምት ወራት በርካታ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት በመሆኑ፣ የመሰረተ ልማት ዝግጅቶችን በማጠናከር የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠናከረ ይገኛል።
በተጨማሪም የኮንፈረንስ (MICE) ቱሪዝምን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት ቀደም ሲል በአዲስ አበባ በዓመት ከ30 እስከ 40 ይካሄዱ የነበሩ ዓለም አቀፍ ሁነቶች፣ በተጠናቀቀው ዓመት ወደ 220 ማደጋቸውተገልጻል።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመቀናጀትም በየዓመቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በኩል የሚያልፉ ከ20 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ7 ቀን ነፃ የቪዛ እድል በመስጠት የእግረ መንገድ (Stopover) ቱሪዝምን ለማስፋፋት እየተሰራ ይገኛል።
