ተማሪዎች የሀገራቸውን ቅርስ፣ ታሪክና ባህል የሳይንስ እውቀቶችን በተግባር እንዲያዩ ለማድረግ ያለመ የጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሄደ።
 
የቱሪዝም ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 46ተኛ ጊዜ በአገራችን ለ 38ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም ቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በትምህርት ቤቶች ባካሄደው ተንቀሳቃሽ የቱሪዝም ዓውደ-ርዕይ ላይ ተሳትፎ በማድረግ አስተዋፆ ላበረከቱ ተማሪዎች የሀገራቸውን ቅርስ፣ ታሪክ፣ ባህል እና ሳይንስ መካከል የተያያዙ እውቀቶችን በተግባር እንዲያዩ ዓላማ ያደረገ የጉብኝት በርሀ-ግብር አድርገዋል።
 
 
ከዳግማዊ ምኒሊክ፣ ከጥቁር አንበሳ፣ ከቦሌ እና ከጄኔራል ታደሰ ብሩ አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው ሀብቶች መካከል የአርኪዮሎጂ እና የፓሊዮንቶሎጂ ቦታዎች አንዱ በሆነው በላይኛው አዋሽ ሸለቆ የሚገኝ እና ከሁለት ሚሊዮን ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ የቅድመ ታሪክ ቦታ የሆነው መልካ ቁንጡሬ ባልጩት ስፍራ እና የጢያ ትክል ድንጋይ መገኛ መካነ ቅርስ ጎብኝተዋል።
 
በጉብኝቱ ላይ ተሳትፎ ያደረጉ ተማሪዎች በትምህርት የሚያውቋቸውን ታሪካዊ ስፍራዎች በቦታው ተገኝተው መመልከታቸው ይበልጥ ለመረዳት እድሉን እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።
 
 
 
ተማሪ ሚሊያን እንዳለ በመልካ ቁንጡሬ እና ጢያ ትክል ድንጋዮች መካነ ቅርስ ያደረገችውን ጉብኝት አስመልክቶ የሰጠችው አስተያየት።
ይመልከቱ