ባለፉት ዘጠኝ ወራት የቱሪዝም ዘርፉን እና የሃገር ገፅታን ለመገንባት ያስቻሉ ተግባራት ተፈጽመዋል

በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አሻ ያህያ በቀጣይ በዘርፉ ለዓመቱ ታቅደው ያልተከናወኑ እና አፈጻጸማቸው ዝቅ ያሉ ተግባራትን አማራጭ አፈጻጸም ስልቶችን በመፈለግ እንዲሁም አዳዲስ የመዳረሻ ሥራዎችን የመለየት ተግባራት ተጠናክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ለምክርቤቱ ሪፖርቱን ካቀረቡ በኃላ ከምክር ቤቱ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ በሰጡት ምላሽ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዓለም ኢትዮጵያን በአዲሱ መልኳ እንዲያውቃት ይሰራል ብለዋል፡፡

ዓለም ኢትዮጵያን የሚያይበት መነጽር መለወጥ አለበት ያሉት ሚኒስትሯ በቀጣይ በአዳዲስ የቱሪዝም ገበያን ማፈላለግ እና ኢትዮጵያን ፈልገውና መርጠው የሚያዩዋት ሀገር መሆኗን ማፅናት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ መናገርና ኢትዮጵያን ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል ሲሉም ሰላማዊት ካሳ ጨምረው ተናግረዋል፡፡