የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጃው ጂይዋን ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጃው ጂይዋን ጋር በኢትዮጵያ ቱሪዝምን ለማጠናከር እና ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እንደገለጹት ጎብኚዎችን ከአለም አቀፍ ገበያ ለመሳብ ያለውን ጥረት እና የቻይና ቱሪስቶችን ለመቀበል ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ ሁለቱ ሀገራት በቱሪዝም ዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።