እንኳን ለ2014 የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ

በየአመቱ መስከረም ወር ላይ የሚከበረዉ የኢሬቻ በዓል ዘንድሮም በደማቅ ስነ-ስርዓት ይከበራል፡፡የፀደይ ወራት በኦሮሞ ዘንድ እንደ ዉበት ተምሳሌት ይቆጠራል፡፡ የፈጣሪ ድንቃድንቅ ሥራዎች የሚደነቅበት ወር ነዉ፡፡ ዉጣዉረድ የበዛበት የክረምት ወር አልፎ፤ የተዘራዉ አዝመራ ለፍሬ በቅቶ፤ የሰዉን ልጅ በተስፋ የሚሞላበት ዉብ የሆነ ወር ነዉ፡፡ የፈጣሪ ድንቅ የሽግግርና የተስፋ ወር የሆነዉን የእሬቻ ክብረ በአል መሬሆ፣ መሬሆ እየተባለ የሚደነቅበት የብርሃን እለት ነዉ፡፡

ኢሬቻ ጥንታዊ የአባይ ሽለቆና መስል የኦሮሞ ሕዝቦች ዘንድ ፈጣሪ አምላክ /ዋቃን/ ለማመስገንና ምልጃ ለመጠየቅ የሚከናውን ሥርዓት ነዉ፡፡ ከዚህ ላይ ባሕላዊ ክንዋኔ ሴቶቹ የጎላ ቦታ እንዳላቸዉ ይነገራል፡፡ የኢሬቻ አካሄድ ይበልጡን በአተገባበር ውስጥ የሚታይ ነው፡፡ በዚህ የዋቄፈታና የሃይማኖት ተቋም ውስጥ የእምነቱ መሪዎች /ቃሉዎችና/ አባ መልካዎች ከፍተኛውን ቦታና ድርሻ የያዙ ናቸው፡፡ በቃሉዎች /የእምነቱ መሪዎች አስተምሮና አመራር መቼና የት የኢሬቻ ሥርዓት መፈጸም እንዳለበት ይናገራሉ፡፡ ይህም ከውቅቶች መቀየር ጋር እጅጉን የተቆራኘና የምሥጋና ቀንና ወራት መኖሩን ያሳያል፡፡

በድጋሚ እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ

ቱሪዝም ኢትዮጵያ

Leave a Comment